የንጋት እልፍኝ
Tuesday, September 15, 2015
Saturday, January 25, 2014
ብቻ መዘመር ነው!
እንዴትም አድርጎ ቢሰራህ ካፈሩ፣
አንተ ምን አገባህ ተውለት ለእግዜሩ!
ይልቅ እፍ ብሎ ከትቢያ ላነሳ፣
ምግባር ቢጎልህም ምስጋናን አትርሳ!
የምሬን ነው ጎበዝ! የ ም ሬ ን - ነ ው!
ፈጣሪን ማወደስ ምንጊዜም ለራስ ነው!
እንኳን ስጋ ለብሶ ለሞተልህ ጌታ፣
ገንዘብ ላበደረህ አለህ አንዳች ቦታ!
ደግሞ ስገስፅህ በትዝብት አትየኝ፣
ወዮልኝ ለራሴ!
እንደምክሬ ባልኖር እኔም እንዳንተ ነኝ!
ግን አየህ ወንድሜ፥
በህፃን አንደበት እንኳ ቢነገርም፣
እውነት ስለሆነ ኃይሉ አይቀየርም!
እናም አንተ ጎበዝ!
ስለምክሬ ብዛት መሰናከል ትተህ፣
ብርሃንን ልበስ ከጨለማ ወጥተህ!
እ/ር በድካም መስራቱ ካልቀረ፣
ሰው ለምን ይሞታል እንዳቀረቀረ?
የጨለማው ገዢ ጨርሶ እስኪመታ
አንተ ምን ቸገረህ ቢዘገይስ ጌታ?!
ይልቅ ና ወዳጄ!
ቅጥር እንቀጥር፥በገና እንወጥር፣
ዝማሬ ብቻ ነው ቀኑን የሚያሳጥር!
አንተ ምን አገባህ ተውለት ለእግዜሩ!
ይልቅ እፍ ብሎ ከትቢያ ላነሳ፣
ምግባር ቢጎልህም ምስጋናን አትርሳ!
የምሬን ነው ጎበዝ! የ ም ሬ ን - ነ ው!
ፈጣሪን ማወደስ ምንጊዜም ለራስ ነው!
እንኳን ስጋ ለብሶ ለሞተልህ ጌታ፣
ገንዘብ ላበደረህ አለህ አንዳች ቦታ!
ደግሞ ስገስፅህ በትዝብት አትየኝ፣
ወዮልኝ ለራሴ!
እንደምክሬ ባልኖር እኔም እንዳንተ ነኝ!
ግን አየህ ወንድሜ፥
በህፃን አንደበት እንኳ ቢነገርም፣
እውነት ስለሆነ ኃይሉ አይቀየርም!
እናም አንተ ጎበዝ!
ስለምክሬ ብዛት መሰናከል ትተህ፣
ብርሃንን ልበስ ከጨለማ ወጥተህ!
እ/ር በድካም መስራቱ ካልቀረ፣
ሰው ለምን ይሞታል እንዳቀረቀረ?
የጨለማው ገዢ ጨርሶ እስኪመታ
አንተ ምን ቸገረህ ቢዘገይስ ጌታ?!
ይልቅ ና ወዳጄ!
ቅጥር እንቀጥር፥በገና እንወጥር፣
ዝማሬ ብቻ ነው ቀኑን የሚያሳጥር!
Tuesday, March 26, 2013
ከአቅም በታች መኖር ክልክል ነው!
ሰው ትናንቱን መርሳት፣ነገውን መተውና ዛሬውን መውረስ ሲችል እውነተኛ አቅሙን መጠቀም ይጀምራል፤ሰው ጠላቱን መማር፣ሸሪኩን ማክበርና ወዳጁን ማፍቀር ሲችል ግማሽ አቅሙን ይጠቀማል፤ሰው ስንፍናውን ሲሽር፣ዕውቀቱን ሲመነዝርና ጥበቡን ሲኖር ከስነ-ፍጥረቱ የሚጠበቀውን ፍፁምና ሊሞላ ተቃርቧል፤ሰው ስለሰው ሲያስብ፣ስለዓለማቱ ሁሉ ሲገደውና ስለፍጥረት ፈጣሪ ሲዘምር ግን ያኔ ፍፁም አቅሙን ተጠቅሟል! ፍፁም ሆኗል! አዎ ይህን ማድረግ ይቻላል ከዛሬ አሁን ከአሁንም በዚች ቅፅበት ለራሳችን እንዲህ ብለን ቃል ብንገባስ?
“ከአቅም በታች መኖር አልፈልግም! ‘አትችልም፣አይሆንልህም!’ የሚሉኝን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የሚመጡ ድምፆች ካሁን ጀምሮ ቦታ አልሰጣቸውም! እኔ ዓለምን እንዳበጃት፣እንድገዛትና እንድባረክባት ተፈጥሬያለሁ! አቅም እንዳለኝ ህሊናየ ልቦናየና አካሌ ይመሰክሩልኛል! እንግዲህ የፈረሰውን አድሳለሁ! የተነቀለውን እተክላለሁ! የበሰበሰውን አስወግዳለሁ! ሰው ሆኜ የተፈጠርኩት እንድማር መሆኑ ይገባኛል ስለዚህም ከተፈጥሮ የሚመጣውን የትኛውንም ዕውቀት በንቃት እቀስማለሁ! የተፈጥሮን ሚዛን ለመጠበቅ ከህይወታዊና ህይወት አልባ ፍጥረታት ጋር በተጓዳኝ ቆሜ በወዳጅነት አብሬ እሰራለሁ! እያንዳንዷን የኑሮ ቅንጣት ጊዜ እንደ ልዩ ስጦታ ቆጥሬ በተድላ ስመላለስ የኋላየን ትቼ ወደፊት እየተዘረጋሁ እንደሆነ ይሰማኛል። ሁሌም ሰው ሆኜ በመፈጠሬ ደስ ይለኛል! እንስሳትን አፈቅራለሁ! እፅዋትን አደንቃለሁ! በተራመድኩ ቁጥር፣በተመገብኩ ቁጥር፣በሰራሁኝ ቁጥር ከአሁኔ ጋር ነኝና ፍስሃ በህዋሳቶቼ ሁሉ ይመላል! ፈጣሪ እንዴት ያለውን እውነተኛ ሰላም እንደሰጠኝ በማወቄ ከእንግዲህ ለአምላኬ የሚፈነቅል የምስጋና መዝሙር ነፍሴ ትቀኛለች! ምላሴም እንደቀደሙት ወገኖቿ በበገና፣በድቤና በአታሞ ታጅባ ለፍጥረት ሁሉ ገዥ፣ለሩህሩህና ቸር አምላክ ታዜማለች! ታሸበሽባለች! ትሰጣለች! አሜን! አሜን! አሜን! እልልልልልልልልልልልልልልልል...
ሰውና ተግዳሮቱ
ከባድ ነው የሰው ልጅ በራሱ ጥላ መበርገግ ሲጀምር! አስቸጋሪ ነው የሰው ልጅ በንግግሩ መልሶ ሲሸማቀቅ! ይልቁን ደግሞ ውድመት ነው የሰው ልጅ ከገዛ ልቦናው ጋር ሲቃቃርና ሲተዛዘብ! ቴዎድሮስ ታደሰ 1999 ዓ.ም ካወጣው አልበም ውስጥ ዝምታ የሚለው ዘፈኑ ላይ ሁሌም ስሜቴን የሚይዝ ስንኝ አለ "አቤቱ! የሰው ልጅ ፅናቱ! ትዕግስቱ ብርታቱ!..." እያለ በጥልቅ ስሜትና የሙዚቃ ቅንብር ድምፃዊው ያንጎራጉራል። የዚህ ዘፈን ገጣሚ በሰው ልጅ ተፈጥሮ ውስጥ አንዳች የገባው ነገር ያለ ይመስላል በርግጠኛነት መናገር የምችለው ግን እውነትም ሰው ብርቱ ነው አንዳንዴ ከፈጣሪው ጋር እየተጣላ፣አንዳንዴ ከተፈጥሮ ጋር እየተጋጨ፣ሌላ ጊዜም ከራሱና ከማህበረሰቡ ጋር እየተዋጋ ቆሞ መሄድ መቻሉ ፍፁም የሚያስደንቅ ክስተት ነው።
ሰው ለምን ከፈጣሪው ጋር ይጣላል?
ከመንፈሳዊ እይታ አንፃር ፈጣሪን ተመርኩዘው የተፈጠሩ አራት ዓይነት ቡድኖች መኖራቸው የታወቀ ነው እነሱም፡-
1. ቴኢስት (በፈጣሪ መኖር የሚያምኑ) 2. ኤቲስት (ፈጣሪ የለም የሚሉ) 3. አግኖስቲክ (ሊኖርም ላይኖርም ይችላል አያገባንም የሚሉ) 4.ግኖስቲክ (ፈጣሪ ዩኒቨርሱ ነው አለ የለም አይሉትም ይኖሩታል፣ይዋሀዱታል እንጂ የሚሉ) ናቸው ምሁራን የትኛውም ሰው ከእነዚህ ከአራቱ ውጭ ሊሆን አይችልም ይላሉ ከእነዚህ ዘርፎች ውስጥ ቴኢስቶች በፈጣሪ ህልውና ስለሚያምኑ ከእርሱ የሚፈልጉትን ባጡ ጊዜ ይሞግቱታል ይከሱታል "እኔ እንዲህ ስሆን ዝም ያልክ እውነት የለህማ!" እያሉ ፀሎታቸውን እስኪሰማ ያማርሩታል! መልስ ካጡም ገሚሱ እንዳኮረፉ በትዕግስት ይጠብቁታል ገሚሱ ይተውታል የቀሩት ወደ ኤቲስትነት ጎራ ዘንበል ሊሉም ይችላሉ ዋናው ነገር ግን የሰው ልጅ እንደ አማኝ ከፈጣሪው ጋር ሊታገልና ሊጣላ እንደሚችል በተለያዩ ሀይማኖታዊ መዛግብት ውስጥ ተመዝግቦ ማግኜታችን ነው።
ሰው ለምን ከተፈጥሮ ጋር ይጣላል?
የሰው ልጅ በተፈጥሮ ውስጥ እንደ አንድ ፍጥረት ቢሆንም የአንበሳውን ድርሻ ወስዶ ተፈጥሮን መልሶ በማፍረስና በመገንባት፣ በመግዛትና በማስተዳደር ለራሱ እንድትመች አድርጎ ሲጠቀምባት ለመኖሩ ከዘመናት በፊት የነበሩና በአርኪዎለጅ ጥናት የተገኙ ስንክሳሮችና ሌሎች ተያያዥ ቁስ አካላት ይጠቁማሉ የዚያኑ ያህል ደግሞ ልክ እንደ የአየር መዛባት፣የውሀ መጥለቅለቅ፣መብረቅና ሰደድ እሳትን የመሳሰሉ የተፈጥሮ አደጋዎች መልሰው የሰው ልጅን ለእንግልት ለስደትና ለሞት ሲዳርጉት እንደኖሩ አሌ የማይሉት እውነት ነው በዚህ ጊዜ ሰው የኖረበትን አካባቢ ረግሞ ወደሌላ መልክዓ ምድር ሄዶ ይሰፍራል ሌላው ሰብዓዊ ፍጡር ከተፈጥሮ ጋር የሚጣላበት መንገድ እንደሚታወቀው ከኢንዱስትሪ አብዮት ጋር በተያያዘ ፋብሪካዎች በሚለቁት የተበከለ ጋዝ ምክንያት ተፈጥሮ አፀፌታዋን የምትመልስበት መንገድ ነው በርግጥ ይሄኛውንም የአረንጓዴ ፖሊሲ በማርቀቅ ጠቡን የማርገብ እድል አለ ከተፈጥሮ ተጣልቶ ከተፈጥሮ ጋር በመታረቅ።
ሰው ለምን ከማህበረሰብ ጋር ይጣላል?
ይሄኛው የሰው ልጅ ከራሱ መንጋ ጋር የሚያደርገው ተጋድሎ የሚፈጠረው ያስማማኛል ብሎ ባረቀቀው በራሱ ህግ፣ስርዓት፣ደንብ፣ ባህልና ወግ መሆኑ አስገራሚ ነው ከእንስሳት ውስጥ ከራሱ መንጋ ጋር የሚጣላ የሰው ልጅ ብቻ ነው ያውም የሚያስብ እንስሳ ሆኖ! በአንድ አካባቢ የሚያግባቡ ልማዶቹ በሌላኛው መንደር ነውርና አስፀያፊ ሆነው የሚገኙበት አጋጣሚ ብዙ ነው እዚህ ጋ ሰው የሚለውን
ስም እንደ ግለሰብ እየተጠቀምኩ እንደሆነ ልብ ይሏል። ሰው ከቤተሰቡ ከአካባቢውና ከማህበረሰቡ ጋር የሚፈጥራቸው መስተጋብሮች መልካም እንዲሆኑ የሚፈልገውን ያህል ጥቅሙ ሲነካበት የገዛ ወገኖቹን በመተው እልፍ ሲል የማሴርና የማጥቃት ዝንባሌ ሊታይበትም ይችላል ወግና ስርዓት ከሚፈጥረው አወንታዊና አሉታዊ ተፅዕኖ ባሻገር የሰው ልጅ በአካላዊ ጉዳትና በስነ ልቦናዊ እክል በዙሪያው ካሉት ሌሎች ሰብዓዊ ፍጡራን ጋር ሊጋጭ ብሎም በህይወትና በንብረት ላይ ውድመት ሲፈጥር ይታያል
ሰው ለምን ከገዛ ራሱ ጋር ይጣላል?
ሰው እንዳሰበው መጠን፣እንደአቅሙ መጠን፣እንደሚገባው መጠን መኖር ሳይችል ሲቀር ከራሱ ጋር ሊጣላ ይችላል ደግሞ ሰው ያለውን ሙሉ ግብዓት ተጠቅሞ ከተሳካለትና ክብርና ዝና ካተረፈ በኋላም በድንገተኛ እክል የነበረውን አሴት እንዲሁም በዙሪያው ያለውን ድጋፍ ሲያጣ ማንነቱን ሊጠላ ብሎም ራሱን እስከማጥፋት ሊደርስ ይችላል። ከዚህ ሀሳብ ጋር በተያያዘ ከኧርቪንግ ዋላስ "የደፈረሰ እንባ" መፅሀፍ መገባደጃ ላይ እንዲህ የሚል ቃል ሰፍሮ ይገኛል "በዚች ዓለም ማጣት የሰው ልጆችን ያሳዝናል ከዚህ የሚልቀው ግን አግኝቶ ማጣት ነው"። ሰዎች ለመኖር መብላት ትተው ለመብላት ሲኖሩም ይሰላቹና ተስፋ ይቆርጣሉ ሰዎች ለሌሎች የመኖር ዝንባሌን ከተፈጥሮ እንደተቸሩት የስነ ልቦና ባለሞያዎች ደጋግመው የሚነግሩን እውነት ከመሆኑ አንፃር መሰረታዊ ፍላጎታቸው ቢሟላም ለሰው ልጅ የሚበጅ ነገር አላደረግንም ብለውም ነፍሳቸውን ሊፀየፏት ይችላሉ በዋነነት ግን የሰው ልጅ ከገዛ ራሱ ጋር የሚጣላው ማህበረሰቡም ሆነ የገዛ ህሊናው የሚያወግዘውን ድርጊት ፈፅሞ በሚገኝበት ጊዜ ነው ያም ለምሳሌ አባት በገዛ ሴት ልጁ ላይ ወሲባዊ ትንኮሳ ሲፈፅም፣እናት ከአቅም በላይ በሆነ ችግርም ቢሆን የወለደችውን የአራስ ቤት ልጇን ስትጥል፣የሀገር መሪ በርካሽ ጥቅም ዜጎቹን ለባዕድ ባርነት አሳልፎ ሲሰጥና በሌሎች መሰል አስነዋሪ ጉዳዮች የሰው ልጅ ሲሳተፍ ቆይቶ ወደ አዕምሮው ሲመለስ ሞቱን አጥብቆ ይመኛታል።
መፍትሄ ይኖር ይሆን?
(የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ ሳይንሳዊ መላምቶችን ጠቅሶ ሳይሆን በራሱ መረዳት ከገባው ነገር ተነስቶ መፍትሄ የሚለውን ለውይይት ያቀርባል)
የሰው ልጅ ከፈጣሪ፣ከተፈጥሮ፣ከማህበረሰብና ከገዛ ራሱ ጋር ያለበትን ተግዳሮት በጥቂቱም ቢሆን ከላይ አይተናል። ሰው ለመንፈሳዊና አካላዊ ማንነቱ ሀላፊነት መውሰድ አለበት የሚል እምነት አለኝ ፈጣሪ ያደርግልኛል ካለ በእምነት በመጠበቁ ለሚደርስበት ነገር ራሱን ማዘጋጀት ይኖርበታል። እኔ የራሴ አምላክ ነኝ የሚል ኢ አማኝ ከሆነም ለሚደርስበት የትኛውም ከባድ ሸክም ራሱን ይፈትን። ነገር ግን በደስታው ጊዜ ሀላፊነቱን ወስዶ ሲቸገር ያልነበረ ጌታውን ፈልጎ የሚወቅስ ከሆነ ያ ሰው ምክንያታዊ አይደለም ማለት ነው። ሰው ከተፈጥሮ ጋር ባለው መስተጋብር የሚፈጠሩ አሉታዊ ግብረመልሶችም እንዲሁ "መስጠትና መቀበል" በሚለው ህግ ሊዳኙ ይገባል እንጅ ተፈጥሮን የማራቆት የትኛውም ቅንቅስቃሴ ራስን ማራቆት መሆኑን ማንም ለማንም አይነግረውም። በአንፃሩ ከማህበረሰብ ጋር ያለው ሰብዓዊ ግጭትም የሚፈታው ህግጋትንና ስርዓትን በመደርደር የሚመጣ ሳይሆን የገዛ ተፈጥሯችንን በመረዳት፣በልቦናችን የተፃፈውን ህግ በማንበብና ፍቅርን በመላበስ የሚፈታ ይመስለኛል። በዋናነት ይህ ሁሉ ችግር እየተፈጠረ ያለው ማለት ሰው ከፈጣሪ፣ከተፈጥሮና ከማህበረሰብ ጋር የሚገጥመው ተግዳሮት ከባድ የሆነበት ምክንያት ከገዛ ራሱ ጋር መስማማት ስላልቻለ ነው ሰው ሰውነቱን የምሩም አምኖ ቢቀበል ከእንስሳት መንጋ በተሻለ እንጅ ባነሰ ሁኔታ እርስ በራሱ ሊጋጭና ሊባላ ከቶውኑ ባልቻለም ነበር። የሚሆነው ነገር መሆን ስላለበት ይሆናል ስንል ህይወት እንድትመራን ፈቅደናል አንዳንዱ ነገር በእኛ ስንፍና ሳይሆን ቀርቷል ስንል ደግሞ ህይወትን መስመር ልናስይዛት ይገባል። ያኔ ለውድቀታችንም ለስኬታችን ሀላፊነት ስለምንወስድ ፈፅሞ ከራሳችንም ሆነ በዙሪያችን ካሉ ኃይላት ጋር ልንጣላ አንችልም ከዩኒቨርሱ ጋር በስምምነት፣በፍቅርና በተድላ አብረን እንፈሳለን እንጅ።ሻሎም።

ሰው የገዛ ራሱ ጠላት ነው?
አዎ ሰው የራሱ ጠላት ነው ባይ ነኝ መቼስ እኔም ሰው አይደለሁ ?
ይሄዋ ልቤ 'ስብጭትጭት' ያደርገኛል እኔን መስማት ጥሎ ያፌዝብኛል እንዳውም ዛሬ ልቤን ልብ ብየ "ትልቅ ስህተት ሰራሁ!" ብለው ልቤ መልሶ "አሄሄሄ ...ያንተ ነገር! መቼ ልክ ሆነህ ታውቅና ነው ተሳሳትኩ የምትለኝ!?" ብሎኝ አረፈው! መቼም ልብ ያላቹህ የልብን ነገር ታውቁታላቹህ! እንዴት ብግን አልኩኝ መሰላቹህ! ቆይ "ጆሮ ለራሱ ባዳ ነው!" የሚሉት ፈሊጥ ሰው ለራሱ ለሚያስበውና ለሚናገረውም ባዳ መሆኑን ጨምሮ የሚገልጥ አባባል ነው እንዴ? እስኪ ይታያቹህ? ሰው እንዴት ከራሱ ጋር ይጣላል? ለነገሩ ሊጣላም ይችላል! ነገር ግን የዚህን ያህል? የእኔን ልብ ያህል? ሰምታችሁልኝ የል ያለኝን? እኔ ነኝ ጥፋተኛው ልብ አለኝ ብየ እንደ ንስሃ አባት ቆጥሬ ለሱ ሀጥያቴን መናዘዜ! አጠፋሁኝ ተሳሳትኩኝ ማለት ለፌዝ ይዳርጋል እንዴ! "አንተ መቼ ልክ ሆነህ ታውቅና ነው!..." አለኝ እኮ!
በነገራችን ላይ የሰራሁት ስህተት ራሱ ይህን ያህል የሚያዘብትም አልነበረም ምን እንደሆነ ታውቃላቹህ ? የልጄ እናት ባለቤቴ ሌላኛውን/ዋን አቡሽ/ሚሚ ልትወልድ አስባ ስላረገዘች 'ያን ነገር' ማግኜት ስላልቻልኩ ሌላ ቦታ ላይ ወድቆ ባገኜው አፈፍ አደረኩት በቃ ይህ ብቻ እኮ ነው ጥፋቴ! አሁን በሚስቴ ሞት፡ ይሄ ትልቅ ነገር ሆኖ ነው? ስንቱ አባወራ እክል ሲገጥመው የሚያደርገው ተራ ስህተት አይደል እንዴ? አያቹህ የኔ ልብ ግን 'አካብዴ' ቢጤ ነው። አሁን እናንተ ጋር እያወራሁ እንኳ እንዴት እንደሚያሽሟጥጥብኝ ብታዩት እንዴት እኮ እንዴት እንደሚያበሽቅ ባወቃቹህልኝ! ስሙት ስሙት አሁን ደግሞ ምን እንዳለኝ፡- "አንተ አይደብርህም! ያቺ የምትወዳት ሚስትህ ገና ለገና አርግዛለች ብለህ በመንገድ ያገኘሃትን ምስኪን ሴተኛ አዳሪ መተኛት ነበረብህ!" ወይ ልቤ ዛሬ አልለቀቀኝም። አቦ እንዳታምኑት ይህ ልቤ ተጣልቶኛል ምን መሳላቹህ ወዳጆቼ እርግጥ ነው ልጅቷን መንገድ ላይ ነው ያገኘኋት ግን ስራ ፈላጊ የቤት ሰራተኛ እንጅ ሴትነቷን የምትሸጥ ልጅ አይደለችም! ከፈለጋቹህ እሷን መጠየቅ ትችላላቹህ! እንዴ ሰው በራሱ ልብ እንዲህ ይሸማቀቃል? ቆይ የት ልግባለት? እኔነት ማረፊያው ስጋና ደም ነው ልብም መኖሪያው ደም ውስጥ፡ አዕምሮም ሃሳብ የሚያውጠነጥነው ያው በስጋና ደም ውስጥ ነው መቼም! እና ከዚህ ልበቢስ ልቤ ወጥቼ እንድሄድ ራሴን ማጥፋት አለብኝ ወይ?
እኔ 'ምለው ሰው ከራሱ ጋር ከተጣላ እንዴት ነው ሲጀመር ከሚስቱ ጋር የሚስማማው? ከጎረቤትም ጋር ቢሆን ለመስማማት እኮ ሰው መጀመሪያ ከገዛ ልቡ ጋር ከነፍስና ከመንፈሱ ጋር መስማማት አለበት! ታድያ እንዴት ነው ልቤ ራሱ ከኔ ጋር ሳይታረቅ ከሚስቴ ወግኖ ጭቅጭቅ የሚያደርገኝ? በቅድሚያ እኮ ለምን ሌላ ሴት እንዳማረኝ ልቤ ልብ ብሎ ሊመክረኝና ሊገስፀኝ ይገባ ነበር ያ ባልሆነበት ሁኔታ ከየት አምጥቼ ነው የሌለኝን ታማኝነት ለባለቤቴ የምታመነው? እንዴ! ኧረ የዘንድሮ ልብ ምን ተሻለው? ፍርጃ ነው ውርጃ የጎደለው? (ሳቅ)
እንዳው የሰሞኑን ነገር ተውትና ራቅ ብየ ይህ ልቤ አምና ያደረገኝን ልንገራቹህ፡ ድከም ሲለኝ ያን ሰሞን ሳልፍ ሳገድም ሳንጎራጉር የሰማ የመንደሬው ሰው ሁሉ ለምን ነጠላ ዜማ አትለቅም አሪፍ ድምፅ አለህ እኮ እያሉ መውጫ መግቢያ አሳጡኝ እኔም ማለፊያ ብየ ስራ ከመጀመሬ በፊት አይድል ሾው ልወዳደር መዘገጃጀት ጀመርኩ ያ ነገረኛ ልቤ እንዳደፈጠ ከርሞ ልወዳደር መድረክ ላይ ስወጣ ይስቅብኝ ጀመር ይባስ ብሎ ሰውነቴን ሙሉ የፈራሁ ለማስመሰል በላብ ያርሰው ቀጠለ ማይክ የያዘውን እጄንም ያንቀጠቅጠው ያዘ ! እንዴት ብየ ልዝፈን? ዳኞቹ በመሳቀቅ እንድደፍር ቢያቀረቅሩም ማንጎራጎር አልቻልኩም ሹክክ ብየ ከመድረክ ወረድኩና ልቤን እየረገምኩ አይደረስ የለ ቤት ደረስኩ ታድያ ስረጋጋ የውስጥ ባላንጣየን ምነው? ብለው "የማትችልበትን ዘፍነህ እንዳታዋርደኝ ብየ ነው!" አለኝ ከመድረክ አፍሮ ከመውረድ በላይ ምን ውርደት አለ እናንተየ? እሱ ግን በቃ እንዲህ ነው የኔ ክብር የሱ ሀፍረት ሆኖበታልና ሲፈልግ በሚወዱኝ ሰዎች መሀል ክፉ ያናግረኛል ተው ስለው "አንተ ተው የምልህን መች ተውክና" ይለኛል ቆይ ምንድን ነው እሱ? አብረን አይደል እንዴ የምናስበው? ስሳሳት ለምን ተሎ አይነግረኝም? ብዙ ርቀት ከተጓዝኩ በኋላ ለምን መንገዴን ያሰናክለዋል? ልቤ ሞገደኛው መልስ አያጣም መቼም "እየተዋከብ ውጭ ውጩን እያልክ አልሰማ ብለኸኝ እንጅ እኔስ ተሎ ተሎ ነበር የማስጠነቅቅህ! አንተ ግን ከፈስህ ጋር የተጣላህ ችኩል ነህ ምን ይገርማል ከኔ ጋር ብትጣላ!" ይልልኛል ጥንክርክር ብሎ። መቼም እንግዴህ እናንተ ገብቷቹህ እንደሁ እንጃ እኔ ይህ ልቤ አልገባኝም! ሲፈልግ ራሱን ብፁዕ ያደርጋል ሲሻው እኔን እንደ መፃጉዕ ያኖረኛል። ቆይ ብቸኩልስ? እውነት የራሴ ድምፅ ይጠፋኛል?
አንድ ቀን መኪና ጀርባ ላይ "ጀግና ማለት ራሱን ታግሎ ያሸነፈ ነው!" የሚል ፅሁፍ አነበብኩና ልቤን እህሳ ምን ትላለህ አልኩት "አንተ ግን ፈሪ ስለሆንክ እኔን ታግለህ ማሸነፍ አትችልም!" አለኝ። ግን ቆይ ሰው ራሱን ቢያሸንፍስ ማነው አሸናፊው ማነው ተሸናፊው? ልቤም እኔም ከውጭ ስንታይ አንድ ሰው ነን ከውስጣችን እንዲህ ያለ ጦርነት መነሳቱን ማን ያውቃል? * ወዳጆቼ ይህን ርዕስ ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ! ሻሎም!

Monday, March 25, 2013
"ተፋፍረን ነው እንጂ ሁላችንም አብደናል!"
አዎና! እንዴ? ቀላል ተፋፍረናል!? ቀላል ተፈራርተናል?! ቀላል አብደናል!?
እስኪ ይታያቹህ ስናወራ እንኳ እንዴት እብደታችን ለመደበቅ ስንጨነቅ እብደታችን
እንደ አዲስ እየተገለጠ እየተገለጠ እንደሚሄድ! እስኪ አሁን እንኳ እኔ ይህን ስፅፍላቹህ እንዴት
ላለማበድ ብየ ስለእብደት ስፅፍ እብደቴ እንደገና እየጋለ እየጋለ እንደሚሄድ ባያቹህ!
ግን ያላበዳቹህ ይመስላቹሃል ያላበድኩ ይመስለኛል ጤነኛ የሆናችሁም አይመስላችሁም
ጤነኛ የሆንኩም አይመስለኝም ግን ደግሞ አብደናል እንዳበድንም አውቀናል
ለምሳሌ እኔ እብድ መሆኔን አሳምሬ አውቃለሁ ግን ቂል አይደለሁም ልብሴን አውልቄ
ስንዘላዘል እያያቹህ እንድትስቁ አልፈልግም ለእናንተ የማሳይቹ አካላዊ ገፅታ ጭንብሌ ነው
ስታዩትም ጨዋ ነኝ፣ምክንያቱም አስመሳይ እብድ ነኝ! እናንተስ ብትሆኑ በ'ኔ አይን
ስትታዩ ጨዋ አይደላቹህ? ምክንያቱም ጨዋ እብዶች ናቹህ! አያቹህ? ነገሩማ ታያላቹህ!
አቃቂር ታወጣላቹህ!ግን ልብም አትሉኝ ልብም አልላቹህ! ለምን? እኔም እናንተም
በውስጥ እያበድን በውጭ እየታበይን እየታበይን ስለምንመላለስ ይሆናላ!
ቆይ? ይህን ሁሉ ስለናንተ የምዘበዝበው ምን አግብቶኝ ነው? ስለ ራሴ እንኳ
የሚያገባኝ አይመስለኝም እኮ! ግን በውስጤ ነው ሃሃሃሃሃ አንዱ ምርጥ እብድ እንዲህ
ሲል ተቀኜ፡- "እጅህ ለፈጠረኝ አሜን ላንተ እላለሁ!
እንኳን የኔ 'ምለው እኔም የኔ አይደለሁ!"
አቤት! አቤት! ለይቶለት ያበደ ሰው እንዴት ታድሏል! ይህን ያለ ገጣሚ የለየለት
እብድ መሆን አለበት!
"ተፈራርተን ነው እንጂ ሁላችንም አብደናል!"
ይህን ያለው የዩንቨርስቲ ተማሪም የጓደኛውን ልቅ እብደት አስተውሎ ነበር ለዛም ነው ሌሎች
ሲዛበቱበት እርሱ የተሟገተለት። ግን ይህ ተማሪ የውስጡን ከመናገሩ በቀር ደፍሮ እብደቱን
መግለጥ አልቻለም። ግን ደግሞ በገባን መጠን መኖር አልቻልንምና ልጁም አልቻለበትም። ግን
አብደናል! ግን ደግሞ የማይገለጥ እብደት! ስለዚህ ተፈራርተናል! ስለዚህ ተፋፍረናል!
ያሳዝናል! ያሳዝናል! ራሳችን መግለጥ ተስኖናል!
ጊዜ ማሳለፊያ ባህሎቻችን ይቀየሩልን!
ማልዶ መነሳት ሃላፊነት የሚሰማው ሰው መገለጫ ከሆነ አምሽቶ መግባት የግዴለሽነት መገለጫ መሆኑ ነው
ግን ግን ጊዜን ከመጠቀም አንፃር ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ ከመስራት አኳያ ስናየው ማልዶ የወጣው ሰው
ራሱ ስራውን እስኪጨርስ ቆይቶ አምሽቶ ቢገባስ? ነገሮችን ከአንድ አቅጣጫ ብቻ ማየታችን ዋጋ እያስከፈለን
ያለ ይመስለኛል! ታማኝ ባል ለመባል በጊዜ የሚገባ ባል በሌላ መንገድ ጊዜውን እየተሰረቀም ሊሆን ይችላል።
ሲጀመር ታማኝነት ከልብ የሚመነጭ ነገር ነው እንጅ ለመወስለትና ለመሴሰንማ በጠራራ ፀሀይ ካሉት ሰዓታት
ውስጥ ያሉት ጥቂት ደቂቃዎችም በቂ ናቸው። አንዳንድ የቤት እመቤቶች ግን በዚህ መንገድ ለማየት አልታደሉምና
ፊልድ የሚወጣ ባልንና ስራ አምሽቶ የሚገባ አባወራን ሁሉ በሌላኛው ግዴለሽ አባወራ ምግባር ነው የሚዳኙት።
እስኪ እንዲህ አድርገን እንየው ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስታችን ልብም ዕውቀትም ሰጥቶት መስሪያ ቤቶች በሙሉ
እንደፋብሪካዎቹ ሃያ አራት ሰዓት መስራት ቢጀምሩ እነዚህ የጨዋ ሰዎች መስፈርቶች አፈር የሚበላቸው አይመስላቹህም?!
ሁሉም ባለትዳር ሲቪክ ሰራተኞች የለሊት ተረኛ መሆን ቢጀምሩ ቀናተኛ ሚስቶች ምን ሊውጣቸው ነው?
አያቹህ ሁሌም ከመንግስት አዲስ ነገር ሲመጣ የምንገባበት የሚጠፋን ቀድመን ስለማንዘጋጅ ነው!በዚህ ረገድ
ተረቶቻችንም ሆነ ፈሊጣዊ ንግግሮቻችን ስለኛ ከእኛ ይልቅ ያዉቁልናል "አይሆንምን ትተሽ ይሆናልን አስቢ፣
ፅድቁ ቀርቶ በወጉ በኮነንከኝ፣የባሰ አታምጣ፣ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው፣ሳታማሀኝ ብላኝ..." ይህ ሁሉ ቢሆን ግን
እኛ ሀበሾች የሐሜት በር እንጂ የጊዜ መብረር አይጨንቀንም!ተሳስተን ከመማርም ያለኝ ይበቃኛል ማለት ይቀናናል
አዲስ ህግ ወጥቶ ካልቀየረን በቀር በማህበረሰቡ ያለንን ተቀባይነት የሚያሳጣ አንድም የለውጥ እንቅስቃሴ ውስጥ
መሳተፍ አንፈልግም!
ነገሩ ባህል ከመሰረታዊ ነገሮች በቀር በየዘመኑ የሚቀየር ቢሆንም አንዴ በተበጀ ወግና
ልማድ ተተብትበን "ባህሌን ባህሌን!" ብለን ከማቀንቀን አልቦዘንም ምክንያቱም እኛ "አይነተኛ/ቲፒካል ሀበሾች!"
ነን። ሰውን ማክበር በተለይ ለታላቆቻችን ቅድሚያ መስጠት፣እንግዳ መቀበል፣ለማተብ ማደር፣ሀገርን መውደድ፣ታሪክንና
ቅርስን መጠበቅ እና ሌሎች ባህሎቻን መሰረታዊ ስለሆኑ መቀየር አይገባቸውም ነገር ግን የዛኑ ያህል ከቴክኖሎጅ
መቆራረጥ፣ጊዜን ማባከን (ቡና በመጠጣትና ጫት በመቃም ሊሆን ይችላል)፣ራዕይንና ባለራዕይን ተስፋ ማስቆረጥ፣
የባላባት አስተሳሰብና ሌሎች ችግሮቻችንን ግን ባህል ብለን መንከባከብ አይጠበቅብንም! ደግሞም ይህ ትውልድ
የራሱን ባህል እንዳይገነባ ማሸማቀቅ ተገቢ አይደለም አንደኛ ዘመን ከዘመን አይበልጥም ሁለተኛ በየትኛው ዘመን
"የዛሬ ልጆች አይረቡም!" የሚል አስተሳሰብ እንደነበረ አይካድም። ሁሌም በሁለት ትውልድ መሃል ተቃርኖ
ይኖራል እያረጀ የሚመጣው ትውልድ አዲሱን ትውልድ መተቸቱ የማይቀር ነው የበጎ ባህሎቻችን ቅብብሎሽ ግን
ሁሌም ይቀጥላል ዘመኑ ይዟቸው የሚመጡ ለውጦችም ተለዋዋጭ ባህሎች ላይ ጫና እየፈጠረ መሄዱ አይቀርም።
ዋናው ነጥብ እዚህ ጋ ነው፡- ተለዋዋጭ ባህል እንደላሊበላና አክሱም ወጥ ስራዎች ተጠብቆ መኖር አለበት በሚሉ
ወግ አጥባቂዎች እጅ ሲወድቅ በመሃል ከንቱ ልማዶቻችን አብረው ሲያቆረቁዙን እንዲኖሩ እየፈረዱብን ነው።
ዋናው ነጥብ እዚህ ጋ ነው፡- ተለዋዋጭ ባህል እንደ ላሊበላና አክሱም ወጥ ስራዎች ተጠብቀው
እንዲኖሩ በሚሟገቱ ወግ አጥባቂዎች እጅ ሲወድቅ አደጋ አለው በመሃል ከንቱ ልማዶችም ተሰግስገው እንዲያ
ቆረቁዙን እየፈረዱብን ነውና። በተለይ ጊዜ አጠቃቀማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ በመላሸቅ ላይ ይገኛል እንዳውም
አንድ የውጭ ዜጋ የአንበሳ የከተማ አውቶብስ ቀኑን ሙሉ ተሳፋሪዎችን ይዞ በየሰፈሩ ሲሄድ አይታ "ይህ
ሁሉ ሰው በምን ሰዓት ነው ታዲያ የሚሰራው?" በማለት ትዝብቷን ገልፃለች በሌላ በኩልም መንግስት
በሃያ አራት ሰዓታት ውስጥ ስምንት የስራ ሰዓታትን ብቻ ለስራ ማወጁ ችግሩን ከድጡ ወደማጡ ዘፍቆታል
ስምንት ሰዓት ስራ፣ስምንት ሰዓት እረፍትና ምኝታ ቢሆን ስምንቱ ሰዓትስ የት ገባ? ምናልባት ከሚያስፈልገው
በላይ እየተዝናናን ይሆናል ምናልባት ማህበራዊ ህይወታችንን እያጠነከርን ይሆናል ምናልባትም ጊዜ ተርፎን
"ጊዜ ማሳለፊያ" የሆሊውድ ፊልም እያየን ጫት እየቃምን ወይም ቡና ከነ "ሴረሞኒው" አፍልተን
ተረኛውን ሰው እያማን ይሆናል ግን እነዚህ ባህሎች ከዘመናቸው አልፈው በዚህ ዘመን ቅቡል ሊሆኑ
ይገባ ነበር? እርግጥ ነው በጊዜያቸው ስናደርጋቸው መልካም ትስስርን ይፈጥራሉ ያለጊዜያቸው ደግሞ
ሀገር አቀፍ ስንፍናን የሚፈለፍሉ ጎጂ ልማዶች ናቸው።
እንግዲህ ጊዜን ባግባቡ ለመጠቀም ብሎም ቀንና ለሊት ለመስራት አስተሳሰባችን እስኪቀየር፣
መንግስት "እንፍራስትራክቸሩን" እስኪያሳድግ ማለት መንገድና መብራት በየመንደሩ እስኪስፋፋ፣የምድሪቱ
እርግማን እስኪነሳ እንጠብቅ ይሆን? ከዛሬ የተሻለ ቀን ካለ ይሁና ምን ገዶን?! እስከዛው ግን "ጊዜ
ማሳለፊያ ባህሎቻችን ይቀየሩልን!" የሚል "ስሎጋን" ይዘን ወግ አጥባቂ ወገኖቻችንን ብንሞግታቸውስ?
ባንሞግታቸውስ?(ሳቅ)።
Subscribe to:
Posts (Atom)