Monday, March 25, 2013

"ተፋፍረን ነው እንጂ ሁላችንም አብደናል!"


             አዎናእንዴቀላል ተፋፍረናል!? ቀላል ተፈራርተናል?! ቀላል አብደናል!?

እስኪ ይታያቹህ ስናወራ እንኳ እንዴት እብደታችን ለመደበቅ ስንጨነቅ እብደታችን
እንደ አዲስ እየተገለጠ እየተገለጠ እንደሚሄድእስኪ አሁን እንኳ እኔ ይህን ስፅፍላቹህ እንዴት
ላለማበድ ብየ ስለእብደት ስፅፍ እብደቴ እንደገና እየጋለ እየጋለ እንደሚሄድ ባያቹህ!
ግን ያላበዳቹህ ይመስላቹሃል ያላበድኩ ይመስለኛል ጤነኛ የሆናችሁም አይመስላችሁም
ጤነኛ የሆንኩም አይመስለኝም ግን ደግሞ አብደናል እንዳበድንም አውቀናል
ለምሳሌ እኔ እብድ መሆኔን አሳምሬ አውቃለሁ ግን ቂል አይደለሁም ልብሴን አውልቄ
ስንዘላዘል እያያቹህ እንድትስቁ አልፈልግም ለእናንተ የማሳይቹ አካላዊ ገፅታ ጭንብሌ ነው
ስታዩትም ጨዋ ነኝ፣ምክንያቱም አስመሳይ እብድ ነኝእናንተስ ብትሆኑ ' አይን
ስትታዩ ጨዋ አይደላቹህምክንያቱም ጨዋ እብዶች ናቹህአያቹህነገሩማ ታያላቹህ!
አቃቂር ታወጣላቹህ!ግን ልብም አትሉኝ ልብም አልላቹህለምንእኔም እናንተም
በውስጥ እያበድን በውጭ እየታበይን እየታበይን ስለምንመላለስ ይሆናላ!
       ቆይይህን ሁሉ ስለናንተ የምዘበዝበው ምን አግብቶኝ ነውስለ ራሴ እንኳ
የሚያገባኝ አይመስለኝም እኮግን በውስጤ ነው ሃሃሃሃሃ አንዱ ምርጥ እብድ እንዲህ
ሲል ተቀኜ፡- "እጅህ ለፈጠረኝ አሜን ላንተ እላለሁ!
        እንኳን የኔ 'ምለው እኔም የኔ አይደለሁ!"
አቤትአቤትለይቶለት ያበደ ሰው እንዴት ታድሏልይህን ያለ ገጣሚ የለየለት
እብድ መሆን አለበት!
       "ተፈራርተን ነው እንጂ ሁላችንም አብደናል!"
ይህን ያለው የዩንቨርስቲ ተማሪም የጓደኛውን ልቅ እብደት አስተውሎ ነበር ለዛም ነው ሌሎች
ሲዛበቱበት እርሱ የተሟገተለት። ግን ይህ ተማሪ የውስጡን ከመናገሩ በቀር ደፍሮ እብደቱን
መግለጥ አልቻለም። ግን ደግሞ በገባን መጠን መኖር አልቻልንምና ልጁም አልቻለበትም። ግን
አብደናልግን ደግሞ የማይገለጥ እብደትስለዚህ ተፈራርተናልስለዚህ ተፋፍረናል!
ያሳዝናልያሳዝናልራሳችን መግለጥ ተስኖናል!

No comments:

Post a Comment