አዎ ሰው የራሱ ጠላት ነው ባይ ነኝ መቼስ እኔም ሰው አይደለሁ ?
ይሄዋ ልቤ 'ስብጭትጭት' ያደርገኛል እኔን መስማት ጥሎ ያፌዝብኛል እንዳውም ዛሬ ልቤን ልብ ብየ "ትልቅ ስህተት ሰራሁ!" ብለው ልቤ መልሶ "አሄሄሄ ...ያንተ ነገር! መቼ ልክ ሆነህ ታውቅና ነው ተሳሳትኩ የምትለኝ!?" ብሎኝ አረፈው! መቼም ልብ ያላቹህ የልብን ነገር ታውቁታላቹህ! እንዴት ብግን አልኩኝ መሰላቹህ! ቆይ "ጆሮ ለራሱ ባዳ ነው!" የሚሉት ፈሊጥ ሰው ለራሱ ለሚያስበውና ለሚናገረውም ባዳ መሆኑን ጨምሮ የሚገልጥ አባባል ነው እንዴ? እስኪ ይታያቹህ? ሰው እንዴት ከራሱ ጋር ይጣላል? ለነገሩ ሊጣላም ይችላል! ነገር ግን የዚህን ያህል? የእኔን ልብ ያህል? ሰምታችሁልኝ የል ያለኝን? እኔ ነኝ ጥፋተኛው ልብ አለኝ ብየ እንደ ንስሃ አባት ቆጥሬ ለሱ ሀጥያቴን መናዘዜ! አጠፋሁኝ ተሳሳትኩኝ ማለት ለፌዝ ይዳርጋል እንዴ! "አንተ መቼ ልክ ሆነህ ታውቅና ነው!..." አለኝ እኮ!
በነገራችን ላይ የሰራሁት ስህተት ራሱ ይህን ያህል የሚያዘብትም አልነበረም ምን እንደሆነ ታውቃላቹህ ? የልጄ እናት ባለቤቴ ሌላኛውን/ዋን አቡሽ/ሚሚ ልትወልድ አስባ ስላረገዘች 'ያን ነገር' ማግኜት ስላልቻልኩ ሌላ ቦታ ላይ ወድቆ ባገኜው አፈፍ አደረኩት በቃ ይህ ብቻ እኮ ነው ጥፋቴ! አሁን በሚስቴ ሞት፡ ይሄ ትልቅ ነገር ሆኖ ነው? ስንቱ አባወራ እክል ሲገጥመው የሚያደርገው ተራ ስህተት አይደል እንዴ? አያቹህ የኔ ልብ ግን 'አካብዴ' ቢጤ ነው። አሁን እናንተ ጋር እያወራሁ እንኳ እንዴት እንደሚያሽሟጥጥብኝ ብታዩት እንዴት እኮ እንዴት እንደሚያበሽቅ ባወቃቹህልኝ! ስሙት ስሙት አሁን ደግሞ ምን እንዳለኝ፡- "አንተ አይደብርህም! ያቺ የምትወዳት ሚስትህ ገና ለገና አርግዛለች ብለህ በመንገድ ያገኘሃትን ምስኪን ሴተኛ አዳሪ መተኛት ነበረብህ!" ወይ ልቤ ዛሬ አልለቀቀኝም። አቦ እንዳታምኑት ይህ ልቤ ተጣልቶኛል ምን መሳላቹህ ወዳጆቼ እርግጥ ነው ልጅቷን መንገድ ላይ ነው ያገኘኋት ግን ስራ ፈላጊ የቤት ሰራተኛ እንጅ ሴትነቷን የምትሸጥ ልጅ አይደለችም! ከፈለጋቹህ እሷን መጠየቅ ትችላላቹህ! እንዴ ሰው በራሱ ልብ እንዲህ ይሸማቀቃል? ቆይ የት ልግባለት? እኔነት ማረፊያው ስጋና ደም ነው ልብም መኖሪያው ደም ውስጥ፡ አዕምሮም ሃሳብ የሚያውጠነጥነው ያው በስጋና ደም ውስጥ ነው መቼም! እና ከዚህ ልበቢስ ልቤ ወጥቼ እንድሄድ ራሴን ማጥፋት አለብኝ ወይ?
እኔ 'ምለው ሰው ከራሱ ጋር ከተጣላ እንዴት ነው ሲጀመር ከሚስቱ ጋር የሚስማማው? ከጎረቤትም ጋር ቢሆን ለመስማማት እኮ ሰው መጀመሪያ ከገዛ ልቡ ጋር ከነፍስና ከመንፈሱ ጋር መስማማት አለበት! ታድያ እንዴት ነው ልቤ ራሱ ከኔ ጋር ሳይታረቅ ከሚስቴ ወግኖ ጭቅጭቅ የሚያደርገኝ? በቅድሚያ እኮ ለምን ሌላ ሴት እንዳማረኝ ልቤ ልብ ብሎ ሊመክረኝና ሊገስፀኝ ይገባ ነበር ያ ባልሆነበት ሁኔታ ከየት አምጥቼ ነው የሌለኝን ታማኝነት ለባለቤቴ የምታመነው? እንዴ! ኧረ የዘንድሮ ልብ ምን ተሻለው? ፍርጃ ነው ውርጃ የጎደለው? (ሳቅ)
እንዳው የሰሞኑን ነገር ተውትና ራቅ ብየ ይህ ልቤ አምና ያደረገኝን ልንገራቹህ፡ ድከም ሲለኝ ያን ሰሞን ሳልፍ ሳገድም ሳንጎራጉር የሰማ የመንደሬው ሰው ሁሉ ለምን ነጠላ ዜማ አትለቅም አሪፍ ድምፅ አለህ እኮ እያሉ መውጫ መግቢያ አሳጡኝ እኔም ማለፊያ ብየ ስራ ከመጀመሬ በፊት አይድል ሾው ልወዳደር መዘገጃጀት ጀመርኩ ያ ነገረኛ ልቤ እንዳደፈጠ ከርሞ ልወዳደር መድረክ ላይ ስወጣ ይስቅብኝ ጀመር ይባስ ብሎ ሰውነቴን ሙሉ የፈራሁ ለማስመሰል በላብ ያርሰው ቀጠለ ማይክ የያዘውን እጄንም ያንቀጠቅጠው ያዘ ! እንዴት ብየ ልዝፈን? ዳኞቹ በመሳቀቅ እንድደፍር ቢያቀረቅሩም ማንጎራጎር አልቻልኩም ሹክክ ብየ ከመድረክ ወረድኩና ልቤን እየረገምኩ አይደረስ የለ ቤት ደረስኩ ታድያ ስረጋጋ የውስጥ ባላንጣየን ምነው? ብለው "የማትችልበትን ዘፍነህ እንዳታዋርደኝ ብየ ነው!" አለኝ ከመድረክ አፍሮ ከመውረድ በላይ ምን ውርደት አለ እናንተየ? እሱ ግን በቃ እንዲህ ነው የኔ ክብር የሱ ሀፍረት ሆኖበታልና ሲፈልግ በሚወዱኝ ሰዎች መሀል ክፉ ያናግረኛል ተው ስለው "አንተ ተው የምልህን መች ተውክና" ይለኛል ቆይ ምንድን ነው እሱ? አብረን አይደል እንዴ የምናስበው? ስሳሳት ለምን ተሎ አይነግረኝም? ብዙ ርቀት ከተጓዝኩ በኋላ ለምን መንገዴን ያሰናክለዋል? ልቤ ሞገደኛው መልስ አያጣም መቼም "እየተዋከብ ውጭ ውጩን እያልክ አልሰማ ብለኸኝ እንጅ እኔስ ተሎ ተሎ ነበር የማስጠነቅቅህ! አንተ ግን ከፈስህ ጋር የተጣላህ ችኩል ነህ ምን ይገርማል ከኔ ጋር ብትጣላ!" ይልልኛል ጥንክርክር ብሎ። መቼም እንግዴህ እናንተ ገብቷቹህ እንደሁ እንጃ እኔ ይህ ልቤ አልገባኝም! ሲፈልግ ራሱን ብፁዕ ያደርጋል ሲሻው እኔን እንደ መፃጉዕ ያኖረኛል። ቆይ ብቸኩልስ? እውነት የራሴ ድምፅ ይጠፋኛል?
አንድ ቀን መኪና ጀርባ ላይ "ጀግና ማለት ራሱን ታግሎ ያሸነፈ ነው!" የሚል ፅሁፍ አነበብኩና ልቤን እህሳ ምን ትላለህ አልኩት "አንተ ግን ፈሪ ስለሆንክ እኔን ታግለህ ማሸነፍ አትችልም!" አለኝ። ግን ቆይ ሰው ራሱን ቢያሸንፍስ ማነው አሸናፊው ማነው ተሸናፊው? ልቤም እኔም ከውጭ ስንታይ አንድ ሰው ነን ከውስጣችን እንዲህ ያለ ጦርነት መነሳቱን ማን ያውቃል? * ወዳጆቼ ይህን ርዕስ ሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ! ሻሎም!

No comments:
Post a Comment